‘የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲን’ በተመለከተ ለኮሚሽኑ ሠራተኞች ሥልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናውን መሰጠት ያስፈለገበት ዋና ዓላማ፣ ለኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ስለ ፖሊሲው ዋና ዋና ጉዳዮች እና የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት በተመለከተ ግንዛቤ በመፍጠር የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት መሆኑን በሥልጠናው መድረክ ተገኝተው ሠራተኞችን ሲያወያዩ የነበሩት ም/ ኮሚሽነር መሐሙድ አቡድ ገልጸዋል፡፡
ከተቋማት ሪፎርም ሥልጠና በተጨማሪ ኮሚሽኑ ከተሰጡት ተልዕኮ አንፃር ሠራተኞችና አመራሮች ሥራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ መሥራት የሚያስችሏቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የሪፎርም ሥልጠና ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ኤሊያስ ወዲሻ፣ ፖሊሲው ተግባራዊ ሲደረግ፣ ውጤታማና ዘመናዊ አገልግሎቶች፣ ውጤታማ የመንግሥት ተቋማት አደረጃጀት፤ ብቁ እና ፕሮፌሽናል የመንግሥት ሠራተኞች፤ የተደራጀ እና ወቅታዊ የሆነ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ እና ነጻ፣ ገለልተኛና አካታች የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ይፈጠራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡

