ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ተቋማት ለሚሰሩ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ሰልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡
የሥልጠና መድረኩን የከፈቱት የካማሺ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኃላፊ አቶ ለሊሣ ፈረንጂ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ፓርቲው አጥብቆ እንደሚታገል ገልፀው ፤ መሰል ስልጠናዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና በትብብር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ስልጠናው የሀብት ምዝገባ ስራዎችንና የተማሪዎች የፀረ-ሙስና ክበባትና የሐይማኖት ተቋማት የፀረ-ሙስና ንቅናቄ አሰራርና አደረጃጀቶች ላይ ተኩረቱን ማድረጉ ተመላክቷል፡፡ የሥልጠና መድረኩ በሐብት ምዝገባና በፀረ-ሙስና አደረጃጀቶች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር የፀረ-ሙስና ትግሉን ውጤታማነት ለማሻሻል ያለመ መሆኑን በኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክተሩ አቶ ኤሊያስ ወዲሻ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ባለሙያ አቶ ገሰሰ አገኘሁ እና በኮሚሽኑ የአውታሮች አደረጃጀት ባለሙያ አቶ ሐብታሙ በዛብህ ናቸው ፡፡

