የትምህርት ቤት የሥነ-ምግባር ክበባት ሙስናን የሚቃወም፣ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ትውልድ ለመቅረጽ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
በአሶሳ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስትና የግል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የስነ-ምግባር ክበባት የኮሚሽኑ ባለሙያዎችና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች ጋር በጋራ የክትትልና ድጋፍ ስራ አካሄዱ፡፡
በክትትልና ድጋፉ ወቅት፣ የመልካም ስነ-ምግባር ጠቀሜታ፣ ኩረጃ በትምህርት ጥራት ላይ የሚያመጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳቶች፣ የኩረጃ ዋና ዋና መንስኤዎች፣ ኩረጃን ለመቀነስ የሚያግዙ የመፍትሄ ሃሳቦችን በተመለከተ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡
ድጋፉን ማድረግ ያስፈለገበት ዋናው ዓላማ፣ መልካም ዜጋ ማፍራት፣ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፣ አዎንታዊ እሴቶችን ማሳደግ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ማጠናከር፣ ተማሪዎችን ወደ ሱስ፣ ስርቆት፣ ፀብ እና ሌሎች ጎጂና አልባሌ ድርጊቶች ውስጥ እንዳይገቡ አስቀድሞ ለመከላከል እና ስብዕናቸውን ለመገንባት መሆኑን በምክክሩ ለይ ተገልጿል።
“ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!”
➤ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!
➤ Facebook page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/
➤ Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr
➤ YouTube ☞ https://www.youtube.com/@bgrsethicsanticorruptionco2370
➤ ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/
➤ Email: ☞ bgrseacc2014@gmail.com

