
ኮሚሽኑ የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በመተከል ዞን ስር ለሚገኙ የወረዳ ሥነ-ምግባር መኮንኖች የተቀናጀ የሙስና መከላከያ እስትራቴጂና ስልቶች እንዲሁም የሥነ- ምግባር መለኪያና መመሪያ በሚሉ ይዘቶች የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ማጠቃለያ የስራ መመሪያ የሰጡት የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራር መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጊሳ ዚፍሃ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች በመንግስት የተሰጣቸውን የህዝብና የመንግስትን ሐብት ከምዝበራ የማዳንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ኃላፊነትን በአግባቡ እንዲወጡ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
የኮሚሽኑ የሀብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ በበኩላቸው ስልጠናው የሥነ ምግባር መኮንኖች ደንብ፣ መመሪያንና አዋጀ በመረዳት ስራቸውን እንዲሰሩ ኃላፊነታቸውንም በእውቀት መፈፀም እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
አቶ ኤሊያስ አክለውም ኮሚሽኑ ሙስናና ብልሹ አሰራር በሀገርና በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ሁለንተናዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን እና የአውታሮች አደራጃጀት ባለሙያ አቶ ባዬ በሬንቶ ናቸው፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች መልስና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
መረጃው የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽ መምሪያ ነው፤
