23ኛውን ዓለማቀፍ የፀረሙስና ቀን ለማክበር ቅድመ-ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል…፡፡
ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ! በሚል መሪ ቃል ፣ በዓለማቀፍ ለ23ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ22ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለማቀፍ የፀረሙስና ቀን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የተዋቀረው ኮሚቴ ውይይት አካሄደ፡፡
በዓሉን ማክበር ያስፈለገበት ዋናው ዓላማ፣ የፀረ ሙስና ትግል ዓለም-አቀፍ ትብብር የቃል-ኪዳን ቀን ከማስታወስ ባሻገር፣ የሙስናና ብልሹ አሠራር አስከፊ ገጽታ መላው ህብረተሰብ እንዲገነዘበውና በህብረት ለመታገል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ለማስቻል መሆኑን በኮሚሽኑ የሙስና መከላከል ዳ/ዳይሬክተር አቶ ጊሳ ዚፍሃ በውይይቱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡
23ኛው ዓለምአቀፍ የፀረሙስና ቀን በዓል በክልል-ዓቀፍ ንቅናቄ በህዳር ወር 2019 ዓም በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ይከበራል።
“ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!”
➤ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉ !!!
➤ Facebook page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/
➤ Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

➤YouTube ☞ https://www.youtube.com/@bgrsethicsanticorruptionco2370
➤ ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/
➤ Email: ☞ bgrseacc2014@gmail.com
