ልጆችን በመጥፎ ሥነ-ምግባር ማሳደግ የነገን ትውልድ ለሙስና ማዘጋጀት ነው!

ግንዛቤ ማሻሻያ

ልጆችን በመጥፎ ሥነ–ምግባር ማሳደግ የነገን ትውልድ ለሙስና ማዘጋጀት ነው!

መልካም ሥነ-ምግባር ከሚገነባባቸውና ከሚበለጽግባቸው ሥፍራዎች መካከል ቤተሰብ ቀዳሚው ነው፡፡ ሆኖም ግን ወላጆች አንዳንድ ጊዜ ባለማወቅ ወይም እንደ ተለመደ ባህል በመቁጠር ለልጆቻቸው መልካም ያልሆኑ የሥነ-ምግባር ባህሪያትን ያስተምራሉ።

ከእነዚህም መካከል፤

➤ በተግባር መጥፎ አርአያ መሆን፤ በልጆቻቸው ፊት መዋሸት፣ ሰዎችን ማታለልና ማጭበርበር፣ ሌሎችን በስድብና በንቀት ማናገር፣ ቃል ገብቶ አለመፈጸም፤

➤ ሙስናንና ኢፍትሐዊነትን ማስተማር፤ አገልግሎት ለማግኘት ጉቦ መስጠትን እንደ መፍትሔ ማየት፣ በዘመድና በወዳጅ ትስስር ያልተገባ ጥቅም ማግኘት፣ የሌላ ሰውን መብት ጥሶ የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የመንግሥትን ንብረት ለግል ጥቅም መጠቀም፤

➤ መጥፎ ልማዶችን ማበረታታት፤ ሌሎችን በገንዘብና በማኅበራዊ ደረጃ መመዘን፣ ለሥራ ኃላፊነት እንዳይሰማቸው ማድረግ፣ ያለ ጥረት ጥቅም ማግኘትን ማበረታታት፤

➤ በማኅበራዊ ግንኙነት የሚታዩ ችግሮች፤ ሴትና ወንድ ልጆችን በእኩል አለማየት፣ የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች አለማክበር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት ወይም በማኅበራዊ ሁኔታ ሰዎችን እንዲለዩ ማስተማር፤

ወላጆች ልጆቻቸውን  መልካም ሥነ–ምግባርን በተግባር የማስተማር ኃላፈነትና ግዴታ አለባቸው ! ልጆችን በመጥፎ ሥነ–ምግባር ማሳደግ የነገን ትውልድ ለሙስና ማዘጋጀት ነው!

“ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!”

➤ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን  በተለያዩ  አማራጮች  ይከታተሉ !!!

➤ Facebook page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/

➤ Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

➤ YouTube ☞ https://www.youtube.com/@bgrsethicsanticorruptionco2370

➤ ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/

➤ Email: ☞ bgrseacc2014@gmail.com

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *