ኮሚሽኑ የቀጣይ 5 ዓመታት ዕቅዱን ገመገመ፡፡
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በቀጣይ 5 አመታት (2018—2022ዓ/ም) ሊያከናውናቸው የታቀዱ ስትራቴጂክ ግቦችን ያካተተ ዕቅድ ገመገመ፡፡
ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ ሊያሳኩ የሚያስችሉ የትኩረት መስኮችን ቀርፆ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን እነዚህም በዋናነት ሙስና በመከላከል ዘርፍ፤ የአሰራር ሥርአት ጥናቶች ማካሄድ፣ ለትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታ የሚያግዙ ስልጠናዎችን መስጠት እና የሐብት ምዝገባና ትክክለኛነት ማጣራት ሥራዎችን መሥራት ናቸው፡፡ በቀጣይ 5 ዓመታትም ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ዕቅድ በማቀድ ወደ ሥራ ለመግባት በኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች በማስገምገም እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በራሱ ከሚሠራቸው ሥራዎች በተጨማሪ ከሌሎች ተቋማት ጋር በአጋርነትና በትብብር ለመስራት የሚያስችለው ግብ በዕቅዱ ውስጥ የተካተተ ሲሆን በአጠቃላይ የእቅዱን ተፈፃሚነት የሚያረጋግጥ የክትትልና ግምገማ ስርአትም ተካቷል፡፡
