ኮሚሽኑ በካማሸ ዞን ለሚሰሩ የመከታተያ ክፍል ባለሙያችና የብልፅግና ፓርቲ የስነ-ምግባርና  እንስፔክሽን አመራሮች   ስልጠና ሰጠ ፡፡  

ወቅታዊ መረጃ

ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን መምሪያ፣ በካማሽ ወረዳ እና ካማሽ ከተማ ለሚሰሩ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች እና የብልፅግና ፓርቲ የስነ-ምግባርና  እንስፔክሽን አመራሮች ስልጠና  ሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናው በሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ መመሪያና   በመከታተያ ክፍሎች የስድስት ወር የስራ እንቅስቃሴና አፈጻጸም ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

 

በስልጠናው ኮሚሽኑ በተለይም ከብልፅግና ፓርቲ የስነ-ምግርና እንስፔክሽን አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት መስራት በተቋማት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ቀድሞ በመከላክል ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንደሚያስችል በውይይቱ ማጠቃለያ ተጠቁሟል፡፡

 

ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን የሚያደርገው የድጋፍና የክትትል ስራ በዛይና ሌሎች ወረዳዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *