የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ሥራውን ውጤታማ ማድረግ
- የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣
- ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
- አነስተኛ አደረጃጀት ያለው ተቋም ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣
- በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
- በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት አነስተኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
- አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
- የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
