የሐብት ምዝገባ መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር ሥርዓት መዘርጋት፣

ዳይሬክቶሬት

የሐብት ምዝገባ መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር ሥርዓት መዘርጋት፣

  • የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • በሀብት ምዝገባ መረጃ ማረጋገጥ ሥራዎች ዙሪያ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በየወቅቱ ለይቶ በማጥናት ለውሳኔ ያቀርባል፣
  • የሀብት ምዝገባ መረጃ ማረጋገጥ ጋር በተያያዘ ጥናቶችን በማድረግ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶች፣ ስልቶችን፣ መመሪያዎችና የአሰራር ማንዋሎችን ያዘጋጃል፣ ያሻሽላል፣
  • እንዲረጋገጡ የተለዩ የሐብት ምዝገባ መረጃዎችን ትክክለኛ እና የተሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥልቶችን ይቀይሳል፣
  • ከሐብት ምዝገባ መረጃ ማረጋገጥ ጋር የተያያዙ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በመቀመር እንዲስፋፉ ያደርጋል፡፡
  • የተቀመረውን ተሞክሮ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ በጥናት የተደገፈ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • የተቀመረውን ልምድ ለማስፋፋት ወይም በሥራ ላይ ለማዋል እንዲቻል ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ይሰጣል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *