የሙስና መከላከል ሥራዎችን መከታተል መወሰን ውጤት መገምገም፣ ውስብስብ የጥናት ሥራዎችን  መምራት፣

ዳይሬክቶሬት

የሙስና መከላከል ሥራዎችን መከታተል መወሰን ውጤት መገምገም፣ ውስብስብ የጥናት ሥራዎችን  መምራት፣

  • በቡድን የሚከናወኑ የሙስና መከላከል ሥራዎች በአግባቡ ስለመከናወናቸው ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ውሳኔ ለሚሹ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችን ከውሳኔ ሀሳብ ጋር ለበላይ ኃላፊ በማቅረብ ያስወስናል፣ አፈፃጸሙን ይከታተላል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ የሚከናወኑ አስቸኳይ የመከላከል ሥራዎችን አጥኚ ባለሙያ በመመደብ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ በቀረበው ውሳኔ ሀሳብ ላይ አስተያየት ይሰጣል፣
  • የጥናትና ምክር አገልግሎት ሥራዎችን አተገባበር በሚመለከት ከቡድኖች በሚቀርብ ሪፖርት መሠረት ይገመግማል፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣
  • ጉልህ በሆኑ ክልላዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ጊዜያዊ ቡድን ያቋቁማል፣ የቡድን አባላት የሥራ ኃላፊነት ይወስናል ለቡድኑ ሥራ ውጤታማነት የሚያግዝ ግብዓቶችን ሌሎች እንዲያሟሉ ያመቻቻል፣ የሚካሄዱ ጥናቶችን ይገመግማል፣ በጋራ ያፀድቃል፣ የሚዘጋጁ መድረኮች ላይ የጥናት ውጤቱን እንዲቀርብ ያደርጋል፣ የጥናት ውጤት አተገባበሩን ይከታተላል፣
  • በጥናትና ምርምር ሥራዎች ጋር በተያያዘ ከሌሎች አካላት ጋር በሚደረጉ የሥራ ትብብሮች ቅንጅታዊ ሥራዎች ግንኑነት በመፍጠር ለሥራው ስኬት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፣
  • ጉልህ በሆኑ የመንግስት ፕሮጀክቶች የሚካሄደውን የክትትል ሥራ የቅርብ ክትትል ያደርጋል፣ የተጠናቀሩ መረጃዎችን በመገምገም ለሕትመት እንዲቀርቡ ያስወስናል፣
  • ከሥራው ባህሪ አኳያ ከመደበኛ የጥናት ሥራዎች ወጪ በልዩ ሁኔታ ከበላይ ኃላፊዎች የሚመጡ የመከላከል ሥራዎችን ለማከናወን የሚችል ጊዜያዊ ቡድን/ግብረ ሃይል/ ያደራጃል፣ ስለ ስራው አቅጣጫ ያስይዛል፣ የቡድን ሥራ ይመራል ይከታተላል፣ የጥናት ሪፖርቱን ይገመግማል፣ ያፀድቃል፣
  • በጥናት ውጤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንዲዳብር ያደርጋል፣ ውጤቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
  • በጥናቱ ውጤት መሠረት የተመላከቱ የማሻሻያ ሀሳቦችን አተገባበር በሚመለከት በሚቀርብ የትግበራ እገዛ ድጋፍ ሪፖርት መሠረት ይገመግማል፣ አቅጣጫዎችን ያመላክታል፣
  • በሚካሄዱ ጥናቶች ወቅት ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቁ ሁኔታዎች ሲኖሩ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል እንዲደርስ ያደርጋል፣

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *