“ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊገነቡ ይገባል፡፡” ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ

ዳይሬክቶሬት
“ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሊገነቡ ይገባል፡፡” ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ
*****************************
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በክልሉ በአለም ባንክ የገንዘብ ብድር በመዲናችን አሶሳ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ተፈፃሚ ስለመሆናቸው ይከታተላል፡፡ ከሰሞኑም የክልሉን ከፍተኛ አመራርና ባለድርሻ አካላት ያቀፈ እስትሪንግ ኮሚቴ በከተማችን በግንባታ ላይ ያሉ ጌጠኛ (ኮብል ስቶን)፣ የጥርጊያና የጠጠር መንገዶች ያሉበትን የግንባታ ሂደት ተዟዙሮ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
ምልከታውን ተከትሎ የታዩ ችግሮችን በማረም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ውይይት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከባለሙያዎች፣ የግንባታ ተቆጣጣሪዎች (ከመሃንዲሶች) እና ባለድርሻ አካላት ጋር ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ (የቤ/ጉ/ክ/መ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር) ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር የሚሰራው የአሶሳ ከተማ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ለከተማችን ህዝብ ተጠቃሚነት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በተለይም የከተማችንን ወጣቶች የሥራ እድል እንዲያገኙ በማድረግ፤ የከተማችንን ገፅታ በመቀየርና ውብና ለኗሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ ሚናው እጅጉን የላቀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
አክለውም የክልሉና የከተማችንን ህዝብ ዘለቄታዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እድሎችን ይዘው የሚመጡ መሰል ፕሮጀክቶች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ መከወን እንደሚያስፈልግ ገልፀው፤ ለውጤታማነቱም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና ባለድርሻ አካለት ድርሻ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *