በት/ቤቶች የሚቋቋሙ የተማሪዎች የሥነ ምግባር ክበባት…

ወቅታዊ መረጃ

በት/ቤቶች የሚቋቋሙ የተማሪዎች የሥነ ምግባር ክበባት በመልካም ሥነ ምግባር የታነፀ፣ በራስ ጥረትና ትጋት ለመኖር ጽኑ አቋም ያለው፣ ለኅሊናው፣ ለሕግና ለሀገሩ ታማኝ የሆነ፣ በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የዳበረ ብቁ ዜጋ ለመፍጠር ያግዛሉ ፡፡

የቤ/ጉ/ክ/መ/ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በትውልድ የስብዕና ግንባታ የሞራል እሴት አስፈላጊነት ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ /Social Media/ አጠቃቀም እና የተማሪዎች ሞራል  በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በአሶሳ ከተማ አስተዳደር፣ በኡራ እና አብርሃሞ ት/ቤቶች ለሚገኙ የስነ-ምግባር ክበብ ተጠሪ መ/ራን  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልማሃዲ፣ ትምህርት ቤቶች ትውልድን በመልካመ  ስነ-ምግባር የማነጽ ተግባርና ኃላፊነታቸውን መወጣት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው ኮሚሽኑ በተቻለው አቅም ሁሉ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *