ሕግ፣ ደንብና መመሪያን ተፈፃሚ ማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
ሕግ፣ ደንብና መመሪያን ተፈፃሚ ማድረግ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡
ህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን ከማውጣት ባለፈ ተፈጻሚነታቸውን መከታተል ሙስናና ብልሹ አሰራርን መከላከል የመጀመሪያው መፍትሔ መሆኑን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ገለፁ፡፡
ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት በክልሉ ግብርና ቢሮ በግብርና ምርት ግብዓቶች የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት የሥራ ዘረፍ ላይ የሙስናና ብልሹ አሰራር ስጋቶችን ለመከላከል በኮሚሽኑ የተካሄደ የአሰራር ሥርዓት ጥናት ሪፖርት ለባለድርሻዎች በቀረበበት ወቅት ነው፡፡
በጥናቱ ከግብርና ምርት ግብዓትና ፋይናስ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ የአሰራር ሂደቶችን በግልፅ ያስረዱት በኮሚሽኑ የአሰራር ጥናት ባለሙያ አቶ ሰገድ ስዩም የጥናቱ ዓለማ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል በምግብ እራስን ለማቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝና የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድግ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ጥናቱ በብዙ መልኩ ተቋማችን ከአራት ዓመት በፊት የነበሩ ክፍተቶችን ያሳያል ያሉት የቢሮው የግብርና ኤክ/አገ/የግ ም/ቢሮ ኃለፊ አቶ ፀጋዬ ተሰማ ክፍተቶችን ለመፍታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የግብርና ምርት ግብዓቶች ግብይትን ከባንክ አሰራር ጋር በማስተሳሰር ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን መዝጋታቸውን አውስተዋል፡፡ አሁንም የክፍያ ስርዓቱን ይበልጡን በማዘመን ከሰው ንክኪ በፀዳ መልኩ የግብርና ግብዓቶች ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ በመስራት ላይ መሆኑን ኃላፊው አክለው ታግረዋል፡፡
መሰል ጥናቶች ከቀረቡ በኋላ በጥናቱ በመፍትሔነት የተቀመጡ ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው የድጋፍና የክትትል ስራዎች እንደሚሰሩ የገለፁት ሌላው የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራር መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጊሳ ዚፋህ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *