የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ *******************

ወቅታዊ መረጃ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፈራረመ፡፡
የስምምነት ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት ለክልሉ ልማትና እድገት የበኩላቸውን መወጣት የሚያስችልና ተልዕኳቸውን ለመፈፀም ከፍተኛ ሚና እንዳለው በሰነዱ ተመላክቷል፡፡
ተቋማቱ በስነ-ምግባር ግንባታ፣ በማህበረሰብ ጥናትና ምርምር፣ በስልጠና ሞጁል ዝግጅት፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር፣ በአሰራርና አደረጃጀት፣ በስልጠና ፍላጎት ልየታ እና ሌሎች የኮሚሽኑን ፍላጎት መሰረት ባደረጉ የትብብር መስኮች በጋራ እንደሚሰሩ በሰነዱ ተገልጿል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከዚህ በፊት ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብበር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙንና በርካታ የሙስና መከላከል ስራዎችን መስራቱን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ አስታውሰዋል፡፡ ነገር ግን የስምምነት ሰነዱ በጊዜ ገደብ የተቀመጠ በመሆኑ ሰነዱን አሻሽሎ እንደገና መፈራረም ማስፈለጉን ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር ከሌሎች ተቋማት እና ከህዝብ ጋር በቅንጅት መስራቱ ሙስናን በመከላከል ውጤታማ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝም አክለው ገልፀዋል፡፡
ደ/ር ከማል አብዱራሂም (የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት) በበኩላቸው በስምምነት ሰነዱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የጋራ በሆኑ ጉዳዮች በተለይም በትውልዱ የሥነ-ምግባር ግንባታ እና በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሰነዱን አቶ ያየህራድ አጥናፉ ( የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስና መከታተያ ክፍል ዳይሬክተር) ያቀረቡት ሲሆን፤ የሁለቱ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ለስምመነት ሰነዱ መፈፀም ከወዲሁ ቁርጠኛ እንዲሆኑ አስተያዬት ተሰጥቷል፡፡
የስምምነት ሰነዱን መፈፀም የሚያስችል የጋራ ዕቅድ ቀርቦ በአጭር ጊዜ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንና የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና ባለሙያዎች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ውይይቶች እና ምክክሮች ሲያደርጉ መቆየታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *