የማስጠንቀቂያ መልዕክት!! ሕዳር 09/2019ዓ/ም፤አሶሳ ( የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፍትህ ቢሮ)

-

የማስጠንቀቂያ መልዕክት!!

ሕዳር 09/2019ዓ/ም፤አሶሳ ( የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፍትህ ቢሮ)

ህገ ወጥ ደላላዎች ህገ ወጥ የህትመት ዉጤቶችን ህጋዊ አስመስለዉ በመጠቀም ከቅርብ ጊዜ ወድህ ከገጠር ወደ ከተማ የተካለሉ የገጠር ቀበሌ የነዋሪዎችን መሬት ወረራ በመፈፀም ባለይዞታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ መረጃዎች ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ለሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት እየደረሱ ይገኛሉ።

የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬትም የደረሱትን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ባደረገዉ ክትትል ህገ ወጥ ህትመቶችን በማዘጋጀት ስራ ላይ በማዋል የገጠር መሬቶችን በህገ ወጥ መንገድ ለማይገባዉ ሰዉ በማስተላለፍ በባለመብቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ሰዎችን ይዞ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በማድረግ የምርመራ ሂደቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ላይ ይገኛል።

በተለይም በአምባ 4፤ በአምባ 3፤ በአምባ 6፤ በአምባ 5 ፤ በአምባ 8 እና በአጎሻ ቀበሌዎች ላይ ህገ ወጥ ሰዎች ህገ ወጥ ማህተሞችን አሰርተዉ ጥቅም ላይ በማዋል ከፍተኛ የመሬት ማጭበርበር ስራዎችን እየሰሩ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉ ግለሰቦች እየተበራከቱ በመምጣታቸዉ ባለይዞታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል መረዳት ተችሏል።

በመሆኑም ከላይ በስም በተዘረዘሩት ቀበሌዎች የምትኖሩ የመሬት ባለይዞታዎች ወይም አረንጓዴ ደብተር ያላችሁ የመሬት ባለይዞታዎች በማታዉቁት ሁኔታ የይዞታ መሬታችሁ በህገ ወጥ ሰዎች ትስስር እየተጭበረበረ መሆኑን እየጠቆምን የመሬታችሁን ደህንነት ለመጠበቅና ባለይዞታነታችሁን ለማስጠበቅ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኘዉ መንግስታዊ ተቋም በመሄድ የማረጋገጥ ስራ ልትሰሩ እንደሚገባ እየገለጽን እንደዚህ አይነት ችግሮችን ለመፍጠር ሙክራ የሚያደርጉ ግለሰቦችን ስታስተዉሉ ጥቆማ በመስጠት ለህግ ማስከበር ስራዉ የዲርሻችሁን እንዲትወጡ መልዕክታችንን እያስተላለፍን ህገ ወጥ ድርጊቱን በመፈፀማቸዉ ተጠርጥረዉ ምርመራ እየተጣራባቸዉ የሚገኙት ግለሰቦች ዉሳኔ ሲሰጣቸዉ ዉሳኔዉን እናሳዉቃችኋለን።

“ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፣ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!”

➤ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን  በተለያዩ  አማራጮች  ይከታተሉ !!!

➤ Facebook page ☞ https://web.facebook.com/bgrseacc/

➤ Telegram Channel ☞ https://t.me/bgrseaccpr

➤ YouTube ☞ https://www.youtube.com/@bgrsethicsanticorruptionco2370

➤ ለጥቆማ ☞ Web.☞https://www.bgrseacc.gov.et/

➤ Email: ☞ bgrseacc2014@gmail.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *