የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር በተመለከተ የተሰራ ጥናት ለውይይት ቀረበ…፡፡
በቤ/ጉ/ክ/መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አሰራር በተመለከተ በክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጥናት ባለሙያዎች የተሰራ ጥናት ለኮሚሽኑ ማኔጅመንት ለውይይት ቀረበ…፡፡
በጥናቱ የተካተቱ ጉዳዮች፤በአሽከርካሪዎች፣ በትራፊክ ፖሊሶች፣ በመንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎች እና በእግረኞች የሚፈፀሙ ችግሮችና የአሰራር ጥሰቶች ተለይተው የመፍትሄ አቅጣጫ ተመላክቶላቸዋል፡፡
ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል አሰራሮችን በማጥናት የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ ሰገድ ስዩም፤ በቀጣይ በጥናት የታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

