የተማሪዎች መልካም ስነ-ምግባር ግንባታ ለት/ቤት ብቻ የሚተው ጉዳይ መሆን የለበትም…፡፡
በአሶሳ ከተማ በሚገኘው ሰላም በር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህር የሆኑት ወ/ሮ የሹሜ አድነው፤ የተማሪዎችን የመልካም ስነ-ምግባር ግንባታ ለት/ቤት ብቻ የሚተው ጉዳይ መሆን እንደሌለበት ተናገሩ፡፡
ር/መምህሯ ይህንን ያሉት የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በት/ቤታቸው ተገኝቶ ተማሪዎችን የማስተማርና የመምከር ሥራ በሰራበት ወቅት ሲሆን ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከዚህ ሊማሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በኮሚሽኑ የመልካም ስነ-ምግባር ግንባታ ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል፤ ተማሪዎች ቀጣይ ሕይዎታቸው ውጤታማ እንዲሆን፤ ስርቆትንና ኩረጃን የሚጸየፉ፣ ወላጆቻቸውንና መምህራንን የሚያከብሩ፣ ከአጓጉል ሶሶችና ድርጊቶች የራቁና መልካም ስነ-ምግባር የተላበሱ እንዲሆኑ ለተማሪዎች ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

