ተጠያቂነት ማለት ውሳኔ የመስጠት ሥልጣንና ኃላፊነት ያላቸው መሪዎች እና ሠራተኞች የሚሰጡት ውሳኔ እና የሚወስዱት እርምጃ ለሚያስከትለው ውጤት ሃላፊነት መውሰድን የሚያመለከት መርህ ነው፡፡
በአንድ ተቋም ውስጥ የተጠያቂነት አሰራር ከሌለ፣ በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሃላፊዎችና ሰራ ተኞች የተሰጣቸውን ሃላፊነት እንደወደዱ የሚጠቀሙበትና ሙስናን ለመፈጸም የተመቻቸ ጫካ ይሆናል ፡፡ በርካታ ጥናቶች የተጠያቂነት ስርዓት አለመኖር ከሙስና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለቸው ያመለክታሉ፡፡ በመሆኑም በመንግስት አሰራር ውስጥ ተጠያቂነትን ማስፈን ሙስናን ለመከላከል ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡፡ 
