ኮሚሽኑ የህፃናትንና ወጣቶችን ስዕብና ለመገንባት የሚያስችል ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በትውልድ የስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ከሚሰራቸው ሥራዎች መካከል ለህፃናትና ወጣቶች መልካም ስብዕና የሚገነቡ ስልጠናዎችን በሚሰጠው መሰረት ለ ‘አባ እንየው ውቤ መታሰቢያ’ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መልካም ሥነ-ምግባርን ማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በት/ቤቱ ተገኝተው ሰልጠናውን የሰጡት አቶ ንጋቱ ጌታሁን የስልጠናው አላማ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በመምከርና በማስተማር ከስነ-ምግባር ጉድለት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
