የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
*************
(አሶሳ፤ ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት ልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን እንደገለጹት ባለፉት በ2018ዓ.ም በ3ኛው ሩብ የበጀት ዓመት በየዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት በክልሉ ሁለተናዊ ብልጽናን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በመድረኩም በክልሉ ባለፉት በ3ኛ ሩብ ዓመት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የተገኙ ተሞክሮዎችና የታዩ ክፍተቶች ላይ በመወያየት የትኩረት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#የቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል_የመንግሥት_ኮሙኒኬሽን_ጉዳዮች_ቢሮ

