☞ ለሙስና መከሰት በርካታ ሁኔታዎች ቢኖሩም በመንግስት አሰራር ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት አለመኖር ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ወቅታዊ መረጃ

☞ ለሙስና መከሰት በርካታ ሁኔታዎች ቢኖሩም በመንግስት አሰራር ውስጥ ግልጽነትና     ተጠያቂነት አለመኖር ዋነኞቹ ናቸው፡፡

 

☞ በመንግስት አሰራር  ውስጥ ግልጽነት ማለት ሕዝቡ በመንግስት ውሣኔዎች ላይ በብቃት መሳተፍ እንዲችል ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ማግኘት ሲችል ነው፡፡ ህዝቡ የመረጠው መንግስት በትክክል መስራቱን ለመቆጣጠር የሚችለው ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ሲያገኝ ነው፡፡ በግልጽነት የአሰራር ስርአት ህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ከቻለ አሰራሮች ሁሉ ግልጽ ስለሚሆኑ ለአስተዳደር በደል፣ ለብልሹ አሰራር ወይም ለሙስና ሰለባ አይሆንም፡፡

 

☞ የግልጽነት  አሰራር ህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ከማድረጉም ባሻገር ጉድለቶች እንዲስተካከሉ፣ እርምጃም እንዲወስድ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም የግልጽነት አንዱ መገለጫ የህዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ማረጋገጥ ነው፡፡

 

☞ እያንዳንዱ መሥሪያ ቤት የሚሰጠውን መንግስታዊ አገልግሎት በተመለከተ ምን ዓይነት አገልግሎት፣ በምን መስፈርት፣ ለማን እንደሚሰጥ በዝርዝር የሚያብራራ መመሪያ ማውጣትና ተጠቃሚው ህብረተሰብ ይህንኑ በሚገባ እንዲያውቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

 

☞ ህግ አስፈፃሚው አካል የሚያወጣቸው ፖሊሲዎች የሚያቀርባቸው የሕግ ረቂቆች ወዘተ… ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡ አስቀድሞ የተወያየባቸውና አስተያየት የሰጠባቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡

 

☞ በመንግስት አሰራር ውስጥ የግልጽነት አሰራር ከሌለ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን መረጃ በሚፈልገው ወቅትና መጠን ሊያገኝ አይችልም፡፡ ይህ ደግሞ መብቱን ለመጠየቅና ለማስከበር እንቅፋት ከመፍጠሩም ባሻገር ፈጻሚውን አካል ተጠያቂ ማድረግ አይችልም፡፡ ለምሳሌ በአንድ የግንባታ ፈቃድ ሰጪ ተቋም ውስጥ “ የግባታ ፈቃድ ለማውጣት ሁለት ቀን ይወስዳል” የሚል አሰራር ቢኖርና ለተገልጋዩ ይኸው አሰራር ግልጽ ያልተደረገለት ከሆነ ፈጻሚው አካል የፈለገውን ያህል ቀን ቢያመላልሰው መብቱን መጠየቅና ማስከበር አይችልም፤ ያጉላላውን ሰራተኛም ተጠያቂ ማድረግ አይችልም፡፤ ይልቁንም በሚፈጠረው መንገላታት ለሙሰኛ የመንግስት ሰራተኛ የተጋለጠ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በመንግስት አሰራር ውስጥ ግልጽነትን ማስፈን ሙስናን ለመከላከል አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

☞ የተጠያቂነት አሰራር ማለት ምን ማለት ነው ….?

ይቀጥላል…..

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *