ኮሚሽኑ በካማሽና መተከል ዞኖች ሲያከናውናቸው የነበሩ የድጋፍና የክትትል ስራዎች ውጤት ገመገመ፡፡
ኮሚሽኑ በካማሽና መተከል ዞኖች ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ተቋማት በመገኘት ሲሠራቸው የቆየውን የሙስና መከላከልና የሐብት ምዝገባ ሥራዎች ውጤታማነት ግምገማ አካሄደ፡፡
በሁለቱም ዞኖች ሲሰጡ ከነበረው የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ የግምገማዊ ስልጠና መድረኮች ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን በመድረኩ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች አፈፃፀም ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው ቀርበው ውይይቶች መካሄዳቸውን ተገልጿል፡፡
በፀረ-ሙስና ትግሉ ጠንካራ አቋም ያላቸው የዞንና የወረዳ አመራሮችና የስነ-ምግባር መኮንኖች በተመደቡባቸው ወረዳዎች የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን ክትትልና ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ኮሚሽነር ከማል ሐሰን እንደተናገሩት ከዞንና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ለኮሚሽኑ የቀረቡ ጥያቄዎች በየደረጃቸው መፍትሔ እንዲያገኙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አክለውም የድጋፍና ክትትል ሥራ በክልሉ በሚገኙ ቀሪ ወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

