7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ፣ ዴሚክራሲያዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅ የኮምዩኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት አበክረው እንዲሰሩ    ጥሪ ቀረበ፡፡ 

ወቅታዊ መረጃ

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ፣ ዴሚክራሲያዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅ የኮምዩኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት አበክረው እንዲሰሩ    ጥሪ ቀረበ፡፡

 

የክልሉ ኮምዩኒኪሽን ቢሮ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀ መድረክ፤ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሮችና ጋዜጠኞች በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ፤ ቅድመና ድህረ ምርጫ ሊሰሩ በሚችሉ የህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ስራዎች በሚመለከት ውይይት ተደርጓል፡፡

 

መድረኩን የከፈቱት በክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሃሰን አህመድ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሮች 7ኛውን ሃገራዊ ምርጫ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅትና በትጋት መስራት ከዘርፉ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

 

በመድረኩ ቀጣይ ከዚሁ ጋር ተያይዞ  የኮምዩኒኬሽን ስራዎችን  እቅድ ያቀረቡት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የኮምዩኒኬሽ ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ምርጫው በሕዝብ ዘንድ አመኔታ ያለው ሆኖ በሠላም እንዲጠናቀቅ ሚዛናዊ የህዝብ ግንኙነት፣ የተግባቦትና የሚዲያ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎችንና ውጤቶችን በሚዲያ ተደራሽ ማድረግ  እንደሚገባም  በዚህ መድረክ ተወስቷል፡፡

 

የዘንድሮው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ  በ2018 በግንቦት ወር እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *