በክልሉ ማዕድን ሐብት ልማት ቢሮ አሰራር ስርዓት ላይ የተደረገ ጥናት ለውይይት ቀረበ ፡፡
በቤ/ጉ/ክ የማዕድን ሐብት ልማት ቢሮ የፈቃድ አሰጣጥ፣ እድሳትና ቁጥጥር በተመለከተ በኮሚሽኑ የጥናት ባለሙያዎች የተሰራ ጥናት ለኮሚሽኑ ማኔጅመንት ለውይይት ቀረበ፡፡
የጥናቱን ቡድን የመሩት ወ/ሮ አመለወርቅ ታዬ እንደገለጹት በጥናቱ፣ በቢሮው የታዩ ጠንካራ ጎኖች፤ ለሙስናና ብልሹ አሰራሮች የሚያጋልጡ የአሰራር ክፍተቶች እና የመፍትሄ ሐሳቦች ተካተውበታል፡፡
የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን፣ ማዕድን እንደ ሃገር ብሎም እንደ ክልል ከፍተኛ ሐብት የሚንቀሳቀስበትና ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ዘርፍ በመሆኑ ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች በጸዳ እና ሃገራችንና ክልላችንን በሚጠቅም መልኩ መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ይህ ጥናት በዋናነት በወርቅ ማዕድን ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፣ በቀጣይ በክልሉ የሚገኙ ሌሎች የማዕድን አይነቶች ላይ ጥናቱ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
የጥናቱ ግኝቶች እና የመፍትሔ ሃሳቦች ከክልሉ ማዕድን ቢሮ ጋር የጋራ በማድረግ የቀረቡ ምክረ-ሐሳቦች ተግባራዊ የሚደረጉ ሁኔታ የሚፈጠር ይሆናል፡፡

