በመንግሥት ሥራ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች በሕግ፣ በመርሕ እና በአሠራር የላቀ ሥነ-ምግባር ይጠበቃል..!
የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መልካም ሥነ-ምግባርን በመገንባት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚያግዝ ስልጠና ለሰራተኞቹ ሰጠ፡፡
የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናው የቀረበው በኮሚሽኑ የስልጠና ባለሙያ በአቶ አወቀ ገ/መስቀል ሲሆን በመንግሥት ተቋማት የሥራ ባህል ላይ የሚታዩ ተጨባጭ ሥነ-ምግባራዊ እንከኖች እና የሥራ ሥነ-ምግባር አለማክበር የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ ሰፊ ውይይቶች ተካሂደው የችግሩ ማስወገጃ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል፡፡


