የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

ወቅታዊ መረጃ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ይበልጥ በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን።

የክልሉ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተገመገመ ነው።
አቶ አሻድሊ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ በኩል አበረታች ውጤቶች የታዩበት ነው።

በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ ሥራዎችን እስከታች በማውረድ ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

‎በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የሕዝቡን ጥያቄ የመለሱ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ይህም የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል ነው ያሉት።

‎በግብርና እና በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የተከናወኑ ተግባራትም ሕዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ አቅርቦትን በማሻሻል ገበያ ማረጋጋት መቻሉን አንስተዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በአጠቃላይ በክልሉ የተከናወኑ አበረታች ተግባራትን በላቀ ጥረት በማስቀጠል በአዲሱ በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ርብርብ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

‎አመራሩ በተቀናጀ ሁኔታ የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆን እንዳለበት ማሳሰባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *