ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን የድጋፍና የክትትል ስራዎችን በመስራት ላይ ነው፤

ወቅታዊ መረጃ

 

ኮሚሽኑ በካማሽ ዞን ስር  በሚገኙ ወረዳዎችና ተቋማት ለሚሰሩ የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች  የድጋፍና የክትትል ስራ በመስራት ላይ ነው፡፡

 

የድጋፍና የክትትል ስራው አላማ  የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ውጤታማ የሙስና መከላከልና የሥነ-ምግባር ግንባታ ስራዎችን መስራት እንደሚያስችላቸው የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችና ብልሹ አሰራር መከላከል ዳይሬክተሩ አቶ ጊሳ ዚፍሃ ጠቁመዋል፡፡

 

በዚህ የክትትልና ድጋፍ ስራ  በዞኑ ተቀዛቅዞ የነበረውን የሐብት ምዝገባ ስራን የማነቃቃትና ወደ ስራ የማስገባት ስራ   እንደሚሰራ የገለፁት ሌላው  የኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ    አመራሮችና ሰራተኞች ሐብታቸውንና ንብረታቸውን በማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ከዚህ የድጋፍና የክትትል ስራ ጎን ለጎን በዞኑ የስነ-ምግባርና የሞራል እሴት ግንባታ የግንዛቤ መድረኮች እንደሚዘጋጁ፤ እንዲሁም የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች በተጓደሉባቸውና ባልተሟሉባቸው ወረዳዎችና ተቋማት  የሟሟላት የማስመድብና  ስራዎች እንደሚሰሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

 

ለድጋፍና ክትትል ስራው ውጤታማነት የካማሽ  ዞን ዋና  አስተዳዳሪ አቶ ብጂጋ ፃፊዮ ዞኑ የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *