የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 20 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ 

ወቅታዊ መረጃ

ባለፉት ሶስት ወራት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የዲጂታል የሙስና መረጃ (ጥቆማ) መቀበያ ስርዓት እና በሌሎች አማራጮች ከቀረቡ ጥቆማዎች ውስጥ 20 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

 

ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው የዲጂታል ሙስና ጥቆማ ማቅረቢያ እና በሌሎች አማራጮች በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረት በሩብ ዓመቱ እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰራተኞች መካከል 8 የፅሁፍ፣10 የደመወዝ፣ 2 ስንብት በድምሩ በ20 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

 

በዲጂታል ሙስና ጥቆማ መቀበያ ስርዓት እና በሌሎች አማራጮች 170 ጥቆማዎች/ አቤቱታዎች ቀርበው በ152 ጥቆማዎች እና አቤቱታዎችን ማጣራት ተችሏል፡፡

በሩብ ዓመቱ የብልሹ አሰራር ጥቆማ ከቀረበባቸው የስራ ሂደቶች መካከል የአዲስ ኃይል ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥና አስቸኳይ ጥገና፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል ስብሰባ፣ ከንብረት አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡

 

በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሶስት ወራት የቀረቡ ጥቆማዎች ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ179 በመቶ ያደገ ሲሆን፤ ይህም የዲጂታል የጥቆማ መቀበያ ስርዓቱ መተግበሪያው /Digital Corruption system/ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ያሳያል፡፡

 

በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራርን ለመታገልና እርምጃ ለመውሰድ ተቋሙ አሁንም ቁረጠኛ መሆኑን ገልጾ፤ተገልጋዩ ማህበረሰብ መሰል ችግሮችን ሲመለከት ባለመተባባር እንዲሁም በተዘረጋው ዘመናዊ የሞባይል መተግበሪያ በመጠቆም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *