
ለግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ተማሪዎች የስነ-ምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ የግንዛቤ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የስነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን ወጣቱ የተራማጅ አስተሳሰብ ባለቤት መሆን እንደሚገባው ገልፀው፤ ይህም የወጣትነት ኃይልንና ጉልበትን ለራስ፣ ለሕዝብና ለሃገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ማዋል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም በሃገር ልማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ወጣቱ የድርሻውን በመወጣት የነገይቱን የበለፀገች ኢትዮጵያ በመገንባት ረገድ አሻራውን ማሳረፍ እንደሚጠበቅበት አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ወጣቱ እራሱን በስነ-ምግባር ማነፅ፣ በእውቀት እና በክህሎት ማስታጠቅ ኢትዮጵ አሁን ላይ ከትውልዱ የምትፈልገው አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
