በአፈጻጸም ግምገማው ላይ የተገኙ አባቶች የሐይማኖት ተቋማት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በመራቅ ለተከታዮቻቸው አርዓያ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል ፡፡
በውይይቱ ላይ ተገኝተው መድረኩን የመሩት ም/ኮሚሽነር ዑሳም ሃሊፋ ባስተላለፉት መልዕክት «እዚህ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች ዘርፎ መክበርን፣ ሰርቆ አለማፈርን የሚያበረታታውን አስተሳሰብ እያወገዛችሁ እና ለተከታዮቻችሁ መልካም ሥነ-ምግባርን እያስተማራችሁ፤እናንተም መልካም ተምሳሌት በመሆን ለትውልዱ መልካም ሥነ-ምግባርን ማውረስ ይጠበቅባችኋል » ብለዋል ፡፡


በኮሚሽኑ የሙስናና ብልሹ አሰራሮች መከላከል ዳ/ዳይሬክተር አቶ ገመዳ ቡሊ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት «የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነ ዛሬ በሚሰጡ የመልካም ሥነ-ምግባር አስተምህሮቶች በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች በየተቋሞቻቸው ይህንን ሐላፊነት በመውሰድ ወጣቶችን በመልካም ሥነ-ምግባር የማነጽ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባችሁ » ብለዋል፡፡
