ኮሚሽኑ ከክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የሐብት አስመዝጋዎችን የመረጃ አያያዝ የሚያዘምን አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
ኮሚሽኑ ከክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የሐብት አስመዝጋዎችን የመረጃ አያያዝ የሚያዘምን አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡
ይህ የሐብት ምዝገባ ሥርዓት የሐብት አስመዝጋቢዎችን መረጃ በተደረጀ መልኩ ወደ ኮምፒውተር ቋት በማስገባት፤ በጥራዝ/ በወረቀት ምክንያት የሚፈጠረውን የቦታ ጥበት፣ በሐብት አስመዝጋቢዎች መረጃ ላይ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት የሚደርሰውን አደጋ እንደሚያስቀር ታምኖበታል፡፡
የሐብት ምዝገባ ስርዓት የዘመነ አሰራር ያለበትን ሁኔታ እና እንዴት ተግበራዊ እንደሚደረግ የኮሚሽኑ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ተመልክተዋል፡፡
ኮሚሽኑ የሐብት አስመዝጋቢዎችን መረጃ በዘመናዊ መንገድ ለመያዝ ወደ ስራ መግባቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *