ምክር ቤቱ በብልሹ አሰራር ላይ ተገኝተዋል ያላቸውን ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች አሰናበተ ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 6ኛ ዙር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

 

በዚህ ጉባኤ የፌደራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንበት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መመርመሩን የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጀት  ዘግቧል፡፡

 

በዚህም መሰረት አዱኛ ነጋሳ እና አክሊሉ ዘሪሁን የተባሉ ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በሙስና እና በብልሹ አሰራር ላይ በመገኘታቸውና ሁለቱ ዳኞች በሥራ ላይ በነበሩ ጊዜ ኃላፊነታቸውን ያላግባባ በመጠቀማቸው ምክር ቤቱ የቀረበውን የስንብት ደብዳቤ አጽድቋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *