
ፎረሙ መተጋገዝንና ቀጣይ ስራዎችን በጋራ መስራት፣ ክፍተቶችን በመዝጋት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብን ዋና ዓላማ አድርጎ እንደሚሰራ መድረኩን የመሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መለሰ ኪዊ አስታውቀዋል፡፡
በመድረኩ የፎርሙ አባላት ከመሬት፣ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ ከኦዲት ግኝት አመላለስና ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በታዩ ምልከታዎች ክፍተቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ተጠቁሟል፡፡ መሰል ክፍቶች እንዲታረሙ ምክረ ሃሳቦች መሰጣታቸውንም የገለፁት የፎረሙ አባላት የተሰጡት ምክረ ሃሳቦች ስለ መተግበራቸው አሁንም አካላዊ ምልከታዎችን እና የድጋፍና የክትትል ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
በዚህ መድረክ የክልሉ የሥነ- ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንን ጨምሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ፣ ዋና ኦዲት፣ ሰብአዊ መብት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ሌሎች የዲሞክራሲ ተቋማት ሪፖርታቸው ቀርቧል፡፡
በተለይም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ በክልሉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በሚመለከት በምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ትኩረት አድረጎ መስራት ቢችል፤ የክልሉን መንግስትና ህዝብ ፣ እንዲሁም የክልሉን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንደሚያግዝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን አስተያዬት ሰጥተዋል፡፡
