(አሶሳ ፦ ጥቅምት 19/2017ዓ/ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የፀረ-ሙስናና እንቅስቃሴና የትግሉ መልካም አጋጣሚዎች፣ ስጋቶችና መፍትሔዎቻችው በሚል ፅንስ ሀሳብ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት አደርጓል ።
የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ኢንጅነር ቢፍቱ ጎሹ በአገረ አቀፍ እና በክልል ደረጃ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመዋጋት እንዲያስችል እና ተቋማችን ከብልሹ አሰራር ለመታደግ የተቋማችን ሠራተኞች ግንዛቤ እንድኖራቸው የተዘጋጅ መድረክ መሆኑን በማንሳት የተቋማችን ሠራተኞች ብልሹ አሰራርን በመጠየፍ ስራቸውን በአግባቡ መፈፀም እንዳለባቸው ጠቁመዎል።
አክለውም ኢ/ር ቢፍቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈጥር እንዲሁም እንደሀገርም ሆነ እንደ ክልላችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የሚያስከትል በመሆኑም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ልንፀየፍ ይገባል ብለዎል።
የቢሮው የሰነምግባር መከታተያ ባለሙያ ወ/ሮ አየለች ቄጡ የውይይቱን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱ ላይም ፦ ስለሙስና የሀይማኖት አስተምሮ፣ የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት፣ የሙስና አይነቶች ፣ የሙስና መገለጫዎች፣ የሙስና መንሰኤዎች እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራሮች በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራውና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ስለሚያስከትለው ተፅዕኖ በሰፊው አብራርተዎል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በጋራ በመከላከል መልካም አስተዳደርን ማስፈን ተገቢ እንደሆነ ገልፀዎል።
ዘገባው የክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው





+2
All reactions:
Mengistu Lalo, የቤጉክ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን and 16 others
