የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር በአምባ አስራ አንድ ቀበሌ ከ200 በላይ የማንጎ ችግኞችን ተከሉ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
(አሶሳ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም) የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች እንደ ክልል እና እንደ ሃገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር የሚያግዝ የችግኝ ተከላ በአምባ አስራ አንድ ዳቡስ ተፋሰስ 240 የማንጎ ችግኞችን በመትከል አካሄዱ፡፡
ክልሉ በተያዘውና በአራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ ቃል ከ 7.5 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን እቅድ ለማሳካትም በችግኝ ተከላው ከ40 በላይ የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
እንደ ሃገር 6.7 ቢሊዬን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱ የሚታወስ ሲሆን፤ የሚተከሉ ችግኞችም ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ፣ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከደለል ሙሌት የሚጠብቅ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑ ታምኖበታል፡፡
አቶ ወንድም አገኝ ተስፋዬ (የ RLLP ፕሮጀክት አስተባባሪና የአፈር ጥበቃ ባለሙያ) እንደገለፁት በተጠቀሰው ቦታ ከ10,000 በላይ የማንጎ ችግኝ ለመትከል መታቀዱንና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስም 5,000 የማንጎ ችግኞች መትከል መቻሉን ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *