
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ይህንን ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች ጋር “የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች !!” በሚል መሪ ሐሳብ በአሶሳ ከተማ በተደረገው የህዝባዊ ውይይት መድረክ ላይ ህብረተሰቡ ባነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
በህዝባዊ ውይይት የሚነሱ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አመራሩ በአግባቡ በመለየት፣ በመፍጠር እና በመፍጠን መርህ መመለስ እንደሚገባ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል።
አቶ ኢሳቅ በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በብልፅግና ፓርቲያችን የሚመራው መንግስታችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚገጥሙትን ፈተናዎች በመደመር ዕሳቤ መሰረት ወደ ድል በመቀየር በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።
ክልላችንም በለውጡ መንግሥት በርካታ የልማት ስኬት ማስመዝገብ መቻሉን በአሶሳ ከተማ የተከናወኑና እየተተገበሩ ያሉት የልማት ስራዎች ማሳያ ነው ብለዋል።
አቶ ኢሳቅ በመጨረሻም በህዝባዊ ውይይት የተነሱ የሰላም ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአግባቡ በመለየት፣ በማደራጀት፣ በመፍጠር እና በመፍጠን መርህ አመራሩ የህዝባችንን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ እንደሚገባ ተናግረዋል።
#Benishangul Gumuz prosperity party
