(የቤጉክመ የሥ.ፀ.ሙ.ኮ፤ አሶሳ፣ ህዳር 1/2015) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአለም የፀረ-ሙስና ቀንን ለማከበር ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የዘንድሮው የአለም የፀረ-ሙስና ቀን በሃገራችን ለ18ኛ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ “ሙስናን መታገል በተግባር” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ በክልላችንም የማጠቃለያ ዝግጅቱ ህዳር 30/2015 በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል፡፡
እስከ ህዳር ሰላሳ በሚኖሩት ጊዜያትም በክልሉ ባሉ ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በጥያቄና መልስ ውድድር፣ በኪነ-ጥበብ ስራዎች፣ በፓናል ውይይትና ልዩ ልዩ ኩነቶች የሚከበር ይሆናል፡፡
በዞኖችና በወረዳዎች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት በሚደረግ የሥነ-ምግባር የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችና እና በመልካም ስነ-ምግባራቸው አርዓያ ግለሰቦችም ህዳር 30 በክልል ደረጃ በሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዕውቅናና ሽልማት የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንም በእለቱ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር እያንዳንዱ ግለሰብ ሙስናን በተግባር ከመፀየፍ ሌሎችን እስከመታገል በቂ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችለውን መነሻ የበዓል እቅድ አዘጋጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

See insights and ads
Boost post
You and 3 others
