ባለሙያው የሚሉትን ኖሩ፤
ነገሩ እንዲህ ነው፤ በእለተ ሐሙስ በቀን 04/07/2017 የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል እንደ ወትሮው ሁሉ መንግስት እና ህዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት በተቋሙ ሲወጡ ይውላሉ፡፡
ሰዓታቸው ሲደርስም ማህበራዊ ጉዳያቸውን ለመፈፀም ከቢሮ ወጥተው ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ ድንገት ግን ልብንና አእምሮን የሚፈትን ነገር ላይ የአይናቸው ጨረር መራቸው ፡፡ ብር ነበር ፤ ብር ፤ ብር 26 000 ( ሃያ ስድስት ሽህ) የኢትዮጵያ ገንዘብ፡፡
ከሶስት የስራ ባልደረባቸው ጋር አብረው ሲሔዱ መሬት ላይ ያዩት ነገር፤ እርግጥ ስለመሆኑ አነድ እርምጃ ወደ ኋላ ቀርተው፤ ብር ስለ መሆኑ አረጋገጡ፡፡ አሁን ጉዳዩን ያላስተዋሉት ሶስቱ የስራ ባልደረቦች አንድ፣ ሁለት . . . ሰባት እርምጃዎችን ተራምደው ሂደዋል፡፡
አቶ አወቀ ገ/መስቀል ብሩን በእጃቸው እንደያዙ ፈጠን ፈጠን ብለው ደረሱ . . . እናንተ ብር . . . ብር አገኘሁ ተመልከቱ፡፡ ባልደረቦቹ ቀልድ እንጅ እውነት አልመሰላቸውም አልጠበቁም አላመኑም ፤ እውነትህን ነው . . . አትቀልድ አቶ አወቀ በሚያምኑት እምነት እየማሉ ብሩን ስለማግኘታቸው ተናገሩ፤ አሁን ቀልድ አይደለም የምር ስለመሆኑ ተረጋገጠ፤
በእርግጥ ሰው የሰውን ንብረትና ገንዘብ አጭበርብሮ በሚወስድበት፣ ለጥቂት ገንዘብ ተብሎ ሰዎች የሰውን ህይወት በሚቀጥፍበት በዚህ ሰዓት መሰል ድርጊቶች ሲታዩ ልብ ወለድ እንጅ እውነት አይመስሉም፡፡
የኋላ ኋላ ብሩ ተቆጥሮ መጠኑ ታወቀ የብሩ ባለቤት አድራሻም ተገኘ፤ ባለቤቱም በተገኘው አድራሻ ተደውሎ፣ መጠው የጠፋባቸውን የብር መጠን በቁጥር ተናገሩ ፤ ሃያ ስድስት ሽ ህ ብር፤ ብሩ የላባቸው የሳቸው ነው በምስክር ፊት ገንዘቡ ተሰጣቸው፡፡ በምላሹም ምስጋናቸውን ለአቶ አወቀ ቸሩ፡፡
አወ አቶ አወቀ ገ/መስቀል በብዙ መድረኮች ትውልድን በሥነ ምግባር ለመቅረፅ ስለ መልካም ስነ-ምግባር፣ ስለ ሞራል እሴቶች ብዙ ብለውናል፡፡ ሌብነት (ሙስና) የሞራል መዝቀጥ ፣ ከሰወኛ ስብእና መውረድ መሆኑን ነግረውናል፡፡
አሁን ፈተነናው ለሳቸው ሁኗል፤ እራሳቸውን አሸንፈዋል፤ ፈተናውንም አልፈዋል፡፡ የምንለውን እንኑር ማለት ይሄው አይደል?
ብሩን የጣሉት ግለሰብ ማህበራዊ ህይወቴ ላይ ችግር ይመጣብኛል በማለታቸው አላካተትናቸውም
