የፍትህ አካላት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ጥሪ አቀረቡ፡፡
**************
(አሶሳ፤ ጥቅምት 26/2015) የፍትህ አካላት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ጥሪ አቀረቡ፡፡ አያይዘውም በሥነ-ምግባር በመታነፀ ህዝብና መንግስት የሰጣቸዉን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
ኮሚሽነር መንግስቱ ይህን ያሉት የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን የ2014 የፍርድ ቤቶች መዝገብ ዳሰሳ በማድረግ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚረዳ የታመነበት ሥልጠና ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በተሰጠበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ገዛኸኝ የኔው (በኮሚሽኑ የሥልጠና ኬዝ ቲም ቡድን መሪ) ፍ/ቤቶች ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ተላብሰዉ አገልግሎት በመስጠት የህዝብን አመኔታ ሊያሳድጉ እንደሚገባ ባቀረቡት ሰነድ አስረድተዋል፡፡



See insights and ads
Boost post
የቤ/ጉ/ክ/መ/የሥነ ምግባር እና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን
