ስራ ማህበራዊ፣ ተቋማዊና ግለሰብአዊ እድገትን የሚፈጥረው የጋራ አቅምን በስራ ዲሲፕሊን መምራት ሲቻል ነው፡፡ አቶ ንጋቱ ጌታሁን – በኮሚሽኑ የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ

ወቅታዊ መረጃ
ስራ ማህበራዊ፣ ተቋማዊና ግለሰብአዊ እድገትን የሚፈጥረው የጋራ አቅምን በስራ ዲሲፕሊን መምራት ሲቻል ነው፡፡
አቶ ንጋቱ ጌታሁን – በኮሚሽኑ የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ
በግብረ-ገብ ያልታነፀ የሥራ ባህል የተፈለገውን ዉጤት በተፈለገው መጠን፣ ዓይነት እና ጊዜ ውስጥ ማስገኘት እንደማይችል የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን አስገንዝበዋል፡፡
በቅንነት፣ በበጎ አመለካካት እና አስተሳሰብ ስራዎችን መስራትም ውጤታማነትን እንደሚያረጋግጥና የመልካ አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት ማህበረሰቡ የሚፈልገውን የተሸለ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማድረስ የሚያግዝ መሆኑን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡
በስራ ሂደት የሚሰጡ አስተያየቶችን በቅንነት መቀበል እና ለመታረም ዝግጁ መሆን ስልጡን ከሆነ ´ሲቪል ሰርቫንት ´ የሚጠበቅ መሆኑን ለመከታተያ ክፍሎች አስረድተዋል፡፡ ከስህተት መማርና አዎንታዊ ስሜትም ጤናማ የህይወት ልምምድ እንዲኖረን እንደሚያግዝ ነው አሰልጣኙ የተናገሩት ፡፡
በስራ ገበታ ላይ የሚታዩ ከመንግስት ንብረት አያያዝ፣ ከሰዓት አከባበር፣ ለስራ የሚገባ ክብርና ፍቅር ካለመስጠት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከልም የመከታተያ ክፍሎች በተመደቡባቸው ወረዳዎችና ተቋማት ላይ መስራት እንደሚገባቸው ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የግልገል በለስ ከተማ የሥልጠና መድረክ ላይ ተገልፆል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *