አንድ ትውልድ ትውልዳዊ ፍሰቱን ጠብቆ  በስኬት መጓዝ ይችል ዘንድ፤  ሃገራት ከቁሳዊ ሥልጣኔ  ባሻገር በመንፈስ የሰለጠነ፤ በሥነ – ምግባር የታነፀና ባለራዕይ ዜጋ ያስፈልጋቸዋል – አቶ አወቀ ገ/መስቀል

- ወቅታዊ መረጃ

ለሚሊነዬም ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች የስብዕናና የሞራል እሴቶች ግንባታ በሚል ይዘት  የግንዛቤ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናውን  የሰጡት የኮሚሽኑ  የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል  አንድ ትውልድ ትውልዳዊ ፍሰቱን ጠብቆ  በስኬት መጓዝ ይችል ዘንድ፤  ሃገራት ከቁሳዊ ሥልጣኔ  ባሻገር በመንፈስ የሰለጠነ፤ በሥነ – ምግባር የታነፀና ባለራዕይ ዜጋ ያስፈልጋቸዋል ፡፡  ወጣቱም እራሱን በዚሁ ልክ ማዘጋጀት እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

 

ትውልዱ በአለማዊ (ቁሳዊ) ተፅዕኖ ውስጥ ወድቆ ማንነቱን እንዳይረሳ በመንፈሳዊና በግብረገባዊ ስብዕና  መታነፅ እንዳለበት የጠቆሙት አሰልጣኙ ለዚህም ኮሚሽኑ  የትውልድ የስነ-ምገባር ግንባታን  ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራበት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

 

 

በተያያዘ ዜና  የአቻ ግፊት ወጣቶች ኣላማቸውን ለማሳካት በሚያደርጉት ጥረት የራሱ የሆነ አወንታዊና አሉታዊ ተፅእኖ አለው ያሉት  አቶ አወቀ፤   ጓደኞቻቸውን ሲመርጡ ጥንቃቄ ማደረግ እንደሚገባቸው እና ለኣላማቸው መሳካት የሚጠቅም ባህሪ ያላቸውን ጎደኞች ብቻ መከተል እንዳለባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *