ለሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተሰጠው ስልጠና ብልሹ ሥነ-ምግባርን በማረቅ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሥራ መሳሪያ እንደሚሆን የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ገለፁ ፡፡

ወቅታዊ መረጃ
ለሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተሰጠው ስልጠና ብልሹ ሥነ-ምግባርን በማረቅ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሥራ መሳሪያ እንደሚሆን የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎች ገለፁ ፡፡
ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ስልጠናዎች አጋዥ መሳሪያ ናቸው ያሉት የፓዊ ወረዳ የአስተዳደር ዘርፍ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ ደስታ ተሾመ ናቸው፡፡
ከሰሞኑ በግልገል በለስ ከተማ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተሰጠው ስልጠናም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ቀድሞ ለመከላከልና መዘናጋት እንዳይኖር የሚያግዝ መሆኑን የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ስልጠናው የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያዎችን የማስተማር፣ የመከላከልና ሙስናና ብልሹ አሰራርን የማጋለጥ ሚና የሚያሳድግ መሆኑን የማንዱራ ወረዳ የኢኮኖሚ ዘረፍ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ ጋይም ቁንድ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ የመከታተያ ክፍሎች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት መድረክ ቢያመቻች፣ ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ ቢቻል፣ የግንኙነት አግባብን ማጠናከር እና የሙስናና ብልሹ አሰራር ጥቆማዎች ተፍፃሚነትን የመከታተል ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው በስልጠናው የተሳተፉ የመከታተያ ክፍል ባለሙያዎች አስተያዬት ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *