የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመገምገም ላይ ነው፡፡
ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቃሲም ኢብራሂም ክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አብራርተዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙ ድሎችንና ተሞክሮዎችን እንዲሁም ውስንነቶቸ ላይ በመወያየት የትኩረት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል፡፡
ከክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፅ ለገጻችን እንዲያመች ተደርጎ የተወሰደ፤

