በክልሉ የተቋማት  የአገልግሎት አሰጣጥን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሲቪል ሰርቪሱ ተሃድሶ (‘ሪፎርም’) ድርሻው የጎላ ነው –  ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን

ወቅታዊ መረጃ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሲቪል ሰርቪሱ ማሻሻያ (‘ሪፎርም’) ድርሻው የጎላ መሆኑን የክልሉ  ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

‎ሰው ተኮር ሲቪል ሰርቪስ ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የመንግስት  አገልግሎት አስተዳደር ስርዓት ‘ሪፎርም’ ማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል።

‎ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚህን ወቅት እንደገለጹት ውጤታማ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት አካታችነትና ብዝሃነትን ማስተናገድ የሚያስችል ተቋም ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ብቁና ታማኝ አገልጋይን ለመፍጠር እና ለማዘመን የተጀመሩ ተግባራት የሃገራችንን   ብልፅግና የሚያረጋግጡ በመሆኑ   ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናግረዋል።

‎እንደ ሀገር የሚቀረፁ ስትራቴጂዎችን ዕውን  በማድረግ የተቋሙን ሪፎርም ተግባራዊ ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን   የገለጹት አቶ አሻድሊ፣ የተዘጋጁ  አዋጆች፣  መመሪያዎችና ደንቦች ተግባራዊ እንደሚደረጉም ጠቁመዋል።

‎የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው  የተቋማት ሪፎርም ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር ብልሹ አሰራሮችን እንደሚቀርፍም ገልጸዋል።

‎ሲቪል ሰርቪሱ   ሰው ተኮር ተቋም እንዲሆንና ለሀገር የሚተጉ አገልጋዮችን ለመፍጠር  እንዲያስችል የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅም  አቶ ጌታሁን አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

‎በክልል ደረጃ በተያዘው በጀት ዓመት በስምንት የመንግስት ተቋማት ላይ ሪፎርሙ ተግባራዊ እንደሚደረግም በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

 

 

 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *