‎በማዕድን ሀብት ላይ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ አሠራር ለመከላከል የጀመራቸውን የቁጥጥር ሥራዎች የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ማዕድን ቦርድ አስታወቀ፡፡  

ወቅታዊ መረጃ

‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ቦርድ ትላንት ባካሄደው ስብሰባ  ‎በማዕድን ሀብት ላይ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ አሠራር ለመከላከል የጀመራቸውን የቁጥጥር ሥራዎች የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

 

‎በክልሉ ያለውን የማዕድን ሀብት የአካባቢ ተጽእኖን በቀነሰ እና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ መጠቀም እንደሚገባም ቦርዱ አፅንኦት ሰጥቷል፡፡

 

‎በሌላ በኩል በተለያዩ የማዕድን ዘርፎች ወደ ሥራ ለመግባት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወደ ልማት ያልገቡ ባለሃብቶች ፈቃድ እንዲሰረዝም  ቦርዱ   ወስኗል።

 

‎በተጨማሪም በክልሉ በማዕድን ሀብቶች ልማት ለመሠማራት የቀረቡ አዳዲስ ጥያቄዎችን ተገቢነት መርምሮ ውሳኔ ማሳለፉን የዘገበው  የክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *