22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በክልል አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

ወቅታዊ መረጃ

 

 

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ታሪካዊውን የፀረ-ሙስና ትግል፤ ዓለም አቀፍ ትብብርና የቃል ኪዳን ቀን ከማስታወስ ባሻገር፤ በዕለቱ ሰፋፊ የፀረ-ሙስና ንቅናቄዎችን ማካሄድ፣ ለፀረ-ሙስና ትግሉ የታደሰ ቁመና መፍጠር፣ ሁሉን አቀፍ ትብብር፣ ትስስርና ቅንጅት ማረጋገጥን አላማ ማድረጉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን አስታውቀዋል፡፡

 

ዕለቱ በክልል ደረጃ ከህዳር 15 – 22/2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት ትውልድን በሥነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር! በሚል መሪ ቃል በተዋረድ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለፀረ-ሙስና ትግሉ የማህበረሰብን ግንዛቤ በሚያጎለብቱ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርና የማጠቃለያ መድረኩም ህዳር 25/2018 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ እንደሚካሄድ ነው ኮሚሽነሩ የገለፁት፡፡

 

በሃገራችን ለ21ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህን በዓል ለማሳካትም የኮሚሽኑ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ወደ ስራ መግባት በሚስችላቸው የማስፈጸሚያ ሰነድ ላይ ወይይት አድርገዋል፡፡

 

ሰነዱን ያቀረቡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል ናቸው፡፡

 

አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የዓለም ሀገራት ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ስምምነት (United Nations Anti-Corruption Convention) እ.ኤ.አ ህዳር 29/2003 ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን እንዲሆን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሰረት ላለፉት 21 ዓመታት ቀኑ ሲከበር መቆየቱ ይታወቃል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *