
ኮሚሽኑ በገጠር መንገድ ትስስርና የምግብ ዋስትና ፕሮግራም በግንባታ ሂደት ላይ ባሉ መንገዶች ላይ ምልከታ ማድረጉን ተከትሎ በውጤቱ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የምልከታው አለማም ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል የማህበረሰብን ተጠቃሚነት ማስቀጠል መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሃዲ ተናግረዋል፡፡
በመሰል ፕሮጀክቶች በአሰራር ግልፀኝነት መጓደል እና በአስተዳደራዊ ችግሮች ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶችንም ቀድሞ ማረም ለመርሃ ግብሮች መቀጠል ፈይዳው የጎላ መሆኑን ም/ኮሚሽነሩ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
አክለውም የመንገድ ፕሮጀክቶች አፈጻፀም ማደግ በአካባቢው ያለውን የማዕድን ሃብት በአግባቡ ለመጠቀምና የግብርና ምርቶችን ለተጠቃሚዎች በማድረስ የአካባቢውን ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡
በምልከታው የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባም የምልከታውን ውጤት ያቀረቡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የስነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ኮሚሽኑ በፕሮጀክቶች ላይ የሚያደርገው ክትትል በቂ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸውና የድርሻቸውን እንዲወጡ ያገዛቸው መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎች መሰል የድጋፍና የክትትል ስራዎች በሌሎች መርሃ ግብሮች ላይም ቢተገበር ውጤታማነትን እንደሚያሳድግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
