የኮሚሽኑ የ2015 ዓ/ም አመታዊ አፈፃፀም

ወቅታዊ መረጃ

ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር   በበጀት አመቱ በእቅድ ይዞ ሲሰራባቸው ከነበሩ ተግባራት 84.64 ከመቶ የሚሆነውን በስኬት ማጠናቀቁን ሪፖርቱን በአስተዳደር አባላት በገመገመበት ወቅት አስታውቋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በበጀት አመቱ በክልሉ የሙስና መከላከል ስራዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ አመርቂ ተግባራትን ሲሰራ መቆየቱን ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ ገልፀዋል፡፡

የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና፣ አስቸኳይ የሙስና መከላከል፣ የአሰራር ጥናት ማካሄድና ማማከር፣ የሐብት ምዝገባና ትክክለኛነት ማረጋገጥ እንዲሁም የአውታሮች አደረጃጀት ሲሰራባቸው ከቆዩ አንኳር የሙስና መከላከል  ተግባራት ጥቂቶች ናቸው፡፡

ተቋሙ  በውጤት ተኮር የምዘና ስርዓትም የአፈጻፀም ደረጃው ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *