ኮሚሽኑ የ 2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ::
በሪፖርት ግምገማው ተቋሙ ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው የአስቸኳይ የሙስና መከላከል÷ በሥነ ምግባርና የሞራል እሴቶች ግንባታ÷ በአሰራር ጥናት÷ በሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ÷ በአውታሮች አደረጃጀትና ተያያዥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች የተገኙ ስኬቶች የሚበረታቱና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው መሆኑን ኮሚሽነር ከማል ሃሰን ጠቁመዋል::
የኮሚሽኑ የበላይ አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች በተለይም የኮሚሽኑን አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት÷ እስትራቴጅያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓ መስራት እንደሚገባ የጋራ በማድረግ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል::
የተቋሙን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሚሽኑ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ፉሲል ናቸው::




